Fana: At a Speed of Life!

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ እንዳስታወቀው÷ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ከሐምሌ 1 ቀን 2013 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም 1 ቢሊየን 186 ሚሊየን 297 ሺህ 461 ብር ተሰብስቧል፡፡
ድጋፉ÷ ከሀገር ውስጥ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ ከዳያስፖራ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስጦታ አካውንት ገቢ፣ ከፒን ሽያጭ ገቢና ከ8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎት የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት 2003 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ከሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች በአጠቃላይ 16 ቢሊየን 915ሚሊየን 312 ሺህ 137 ብር መሰብሰቡ ተመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.