Fana: At a Speed of Life!

በአረንጓዴ አሻራ እየተመዘገበ ያለውን ስኬት በገቢ አሰባሰቡ በመድገም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በትጋት እንሰራለን- ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን እና የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በሰበታ አዋስ ደበል ተራራ ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ተክለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ÷የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኮሚሽኑ ሰራተኞች እና አመራሮች የራሳቸውን አሻራ እያሳረፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎን ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን  ነው ያስረዱት፡፡

ʽችግኝ ከመትከል በላይ ማስቀመጥ የምንፈልገው አሻራ፣ ትውልዱ በአንድነት ከቆመ የማንሻገረው ችግር እንደሌለ ማሳየት ነው ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ÷ በአረንጓዴ አሻራ እየተመዘገበ ያለውን ስኬትም በገቢ አሰባሰቡ በመድገም የሀገራችንን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በትጋት እንሰራለን ብለዋል፡፡

ለአራተኛ ጊዜ ከተደረገው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ጎን ለጎን ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የደብተር፣ የቦርሳ እና ሌሎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን አንስተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የጉምሩክ ኮሚሽን እና የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም የኦሮሚያ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አባዱላ ገመዳ መሳተፋቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.