Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ400 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው በጎ አድራጎት ድርጅት ሲ ሴፍ ፒ ኤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፊሊጶስ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ከ400 በላይ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ÷ ከቻይናው በጎ አድራጎት ድርጅት ሲ ሴፍ ፒ ኤ የተገኘ ሲሆን÷ የቦርሳና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው፡፡

ድጋፉንም÷ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እና የቻይናው የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኮንሱላር ያንግ ዪ ሃንግ በወረዳ 11 ተገኝተው ማስረከባቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ተማሪዎችን ማገዝ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መቅረፅ ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንደገለጹት÷ የትውልድ ግንባታ ስራ የሆነውን ትምህርትን መደገፍ የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ በጋራ ተባብረን የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆችን ማገዝ ይገባል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.