Fana: At a Speed of Life!

ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች የጀመሩትን በጎ ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በተንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሰሯቸው በጎ ተግባራት አበረታች በመሆናቸው የጀመሩትን በጎ ስራ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠየቀ፡፡
ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሙና አሕመድን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወይዘሮ ሙና አሕመድ በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ወጣቶቹ በተንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የሰሯቸውን በጎ ተግባራት አድንቀው÷ ወጣቶቹ የጀመሩትን በጎ ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
አቶ አብርሃም ታደሰ በበኩላቸው÷ ወጣቶቹ ለሚያከናውኗቸው ተግባራት የአስተዳደሩ እገዛና ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.