Fana: At a Speed of Life!

ጠንካራ መንግስት በመገንባት ጠላቶቻችንን ማጥፋት ይገባል – ዶክተር ይልቃል ከፋለ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድነታችንን በማጠናከር እና ጠንካራ መንግስት በመገንባት በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በማስቆም ጠላቶቻችንን ማጥፋት ይገባል ሲሉ የአማራ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት ከሰሜን ሸዋ ዞን የሕዝብ ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ሸኔ ባለፉት ሁለት ቀናት በአጣየ እና አካባቢው በፈፀመው ጥቃት÷ ንፁሃንን መግደሉን እና ማቁሰሉን ሀብትና ንብረትም ማውደሙን ገልጸዋል፡፡

ይህን ችግር በአንድ ጀምበር መፍታት ባይቻልም÷ በሕዝብና መንግስት መካከል  ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር እንሻገረዋለን ብለዋል፡፡

ክልሉ ከአሸባሪዎቹ ትህነግ እና ሸኔ ወረራ በኋላ ጠንክሮ በመስራት ከደረሰበት ጉዳት እያገገመ ቢሆንም÷ አሁንም አሸባሪው ሸኔ በሕዝባችን ላይ ጦርነት እየከፈተ ንፁሃን እየቀጠፈ እንዲሁም ሀብትና ንብረትን እያወደመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዚህም አንድነታችንን በማጠናከር እና በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ሆነን ጠላቶቻችንን ማጥፋት ይገባናል ብለዋል ።

በውይይቱ የተገኙ የሕዝብ ተወካዮችም የሰላምና ደኅንነት፣ የመሰረተ ልማት፣ የኑሮ ውድነት እና የመልሶ ማቋቋም ሥራና መሰል ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

በአበበ የሸዋልዑል

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.