Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ በመጪው የፈረንጆች መስከረም 5 አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትሯን ታሳውቃለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመጪው የፈረንጆች መስከረም 5 በይፋ ይታወቃል ተባለ፡፡

ከሀገሪቱ ወግ አጥባቂ ፓርቲ አመራሮች መካከል ተወዳድሮ አሸናፊ የሆነው ከመጪው የፈረንጆቹ መስከረም 5 ቀን ጀምሮ የፓርቲው መሪ እና የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ እንደሚመረጥ ፓርቲው አስታውቋል፡፡

12 የፓርቲው አባላት ለውድድር ለመቅረብ ፍላጎት ያሳዩ ሲሆን የመጨረሻዎቹ ሁለት እጩዎች ፓርላማው ለእረፍት ከመበተኑ በፊት እንዲታወቁ ይደረጋል መባሉን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከጥቂት ቀናት በፊት ከ50 በላይ የመንግሥታቸው ሚኒስትሮች እና የስራ ሀላፊዎች ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸው የሚታወስ ነው፡፡

ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው ግፊት ከፓርቲ መሪነታቸው ለመልቀቅ የተስማሙ ቢሆንም ለተወሰኑ ወራት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመቆየት ፍላጎት እንደነበራቸው ነው የሚነገረው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.