Fana: At a Speed of Life!

 ዱሬሳ ሹቢሳ ባህር ዳር ከነማን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት በይፋ የዝውውር ገበያውን የተቀላቀለው ባህር ዳር ከተማ የመስመር አጥቂውን ዱሬሳ ሹቢሳን በሁለት ዓመት ውል ማስፈረሙን አስታውቋል፡፡

ከአዳማ ወጣት ቡድን የተገኘው ዱሬሳ ሹቢሳ ያለፈውን እና የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሰበታ ከተማ ማሳለፉ ይታወሳል።

አሁን ዳግሞ ከቀድሞ አሰልጣኙ አብርሃም መብራቱ ጋር ለመስራት ባህር ዳር ከነማን ተቀላቅሏል።

ባህር ዳር ከነማ ከዚህ ቀደም ያሬድ ባየህን ያስፈረመ ሲሆን፥ ናይጀሪያዊውን አማካይ ቻርለስ ሪባኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ለማስፈረም በቃል ደረጃ መስማማቱን ሶከር ኢትዮጵያ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

በተጨማሪም ከአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ጋር የተለያየው ኢትዮጵያ ቡና ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። ክለቡ የወልቂጤውን የመስመር አጥቂ ጫላ ተሺታን እንዲሁም የሐዋሳ ከተማውን አጥቂ ብሩክ በየነን በሁለት አመት ውል አስፈርመዋል።

የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው ቅዱስ ጊዮርስም የመስመር አጥቂውን ቢኒያም በላይን የግላቸው አድርጓል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.