Fana: At a Speed of Life!

ሥራ አጥነትን ለመቀነስ የግሉ ዘርፍ የማይተካ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በቅርቡ የሚተገበረውን ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድን ተግባራዊ ለማድረግ ከግል ተቋማት እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር እየተወያየ ነው፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሥራ አጥ ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መሆኑን ጠቁመው ከሚስተዋለው የሥራ አጥ ቁጥር መካከልም÷ 80 በመቶ ያህሉ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች መሆናቸው ተናግረዋል፡፡
ወጣቱን የሥራ ባለቤት ለማድረግ መንግስት ከአጋር አካላትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከል÷ “ ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ፕሮጀክቱ መንግስት ከአጋር አካላትና ከግሉ ዘርፍ ጋር በመሆን የሚተገበር ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ 70 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
ከዚህ ውስጥም ከአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 49 ሺህ ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ተመላክቷል፡፡
በያዝነው የክረምት ወቅት 10 ሺህ 500 ወጣቶችን በ36 ወረዳዎች የሥራ ባላቤት እንዲሆኑ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ስራ እንደተጠናቀቀ መገለጹን የሥራ ኢንተር ፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.