Fana: At a Speed of Life!

በአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ ህዝቡና አመራሩ በንቃት እንዲሳተፉ አቶ አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ እና አመራር በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዘመቻ በንቃት እንዲሳተፉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቀረቡ፡፡

አቶ አሻድሊ ሀሰን ÷ በዘንድሮው የክረምቱ የ”አረንጓዴ ዐሻራ” የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በግላቸው 100 ችግኞችን ለመትከል ማቀዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በክልል ደረጃ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ትኩረት መደረጉን እና ለእዚህም የማንጎ፣ ቡና፣ አቡካዶ፣ ብርቱካን፣ ዘይቱንና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች መዘጋጀታቸው የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ ዝግጅት በተመለከቱበት ወቅት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የችግኝና የተከላ ቦታዎች ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.