Fana: At a Speed of Life!

በሕገ ወጥ መንገድ በመኖሪያ ቤት የተከማቸ መድኃኒት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ ወጥ መንገድ በመኖሪያ ቤት የተከማቸ መድኃኒት መያዙን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

መድኃኒቱ የተያዘው በሕገ ወጥ መንገድ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተከማችቶ ለሽያጭ ሊቀርብ ሲል መሆኑ ተገልጿል፡፡

መድኃኒቱ በባለሙያ የሚታዘዝ ሆኖ ሳለ ባለሙያ ባልሆነ ግለሰብ ቤት መገኘቱ እንዲሁም በምርት ጥራቱ ተጽዕኖ በሚፈጥር መልኩ መከማቸቱን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸው መድኃኒት የተያዘው÷ የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊሲ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ኢንተለጀንስ መምሪያ ጋር ባካሄዱት ዘመቻ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.