Fana: At a Speed of Life!

ግብፅ በሽብር የተከሰሱ 112 ሰዎች የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

አዲስ ሰበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብጽ በሽብር ድርጊት ተሳትፈዋል የተባሉ 112 ሰዎች የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው ፡፡

ግለሰቦቹ በግብፅ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል በመሳተፍ ነው ጥፋተኛ የተባሉት

ተከሳሾቹ በፍተሻ ጣቢያዎች ላይ ጥቃቶችን በማድረስ ፣ ረዳት የህዝብ አቃቤ ህግን ለመግደል ሙከራ አድርገዋል የሚል ክስን ጨምሮ በ14 የወንጀል ድርጊቶች ተሳትፈዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

ግለሰቦቹ ሃዝም የተባለ ታጣቂ ቡድን አባላት ናቸው ነው የተባሉት፡፡

ይህ የታጣቂ ቡድን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በፈረንጆቹ 2013 ከስልጣን የተወገደው የሙስሊም ውድማማቾች ታጣቂ ክንፍ ነው የሚል ግምትን የግብፅ ባለሥልጣናት ያስቀምጣሉ።

ምንጭ÷ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.