Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ሚና በማጎልበት ተተኪ አመራሮችን ለማፍራት ያለመ የስልጠና መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ሚና በማጎልበት ተተኪ አመራሮችን ለማፍራት ያለመ የስልጠና መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

አራተኛውን ዙር የስልጠና መድረክ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኦሞድ ያስጀመሩት ሲሆን÷ በስልጠና መድረኩ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ ሴት አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

ወይዘሮ አለሚቱ ኦሞድ በመድረኩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷ የሴቶች የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ሚና መጎልበት የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት ከመሆኑ ባሻገር የሰብዓዊ መብት ጉዳይ መሆኑን ሁሉም አካላት ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የታቀዱ ግቦችን ተፈፃሚ ለማድረግ በመንግስት መዋቅርና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ለተውጣጡ ሴት አመራሮች ስልጠና በመስጠት ተተኪ አመራር ለማፍራት የበኩሉን እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የስልጠና መድረኩን የሴቶችንና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፕሬዚዳንት ፅህፈት የተመድ ሴቶች ፅህፈት ቤት በጋራ በመተባበር ያዘጋጁት ነው ተብሏል፡፡

የስልጠና መድረኩ ከዛሬ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ እና መሰረታዊ የአመራር ጥበብ፣ የተግባቦትና የግጭት አፈታት ስልቶች፣ ስርዓተ እኩልነትና አመራር፣ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ከሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.