Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኀብረት እስካሁን 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የሩሲያን ሀብቶች አግጃለሁ አለ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በየካቲት 24 ዩክሬን ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የአውሮፓ ኀብረት 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር የሚገመት የሩሲያ ሀብትና ንብረቶችን ማገዱን ኀብረቱ የፍትህ ኮሚሽነር ዲዲየር ሬይንደርስ ተናግረዋል ።
ሬይንደርስ በፕራግ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት፥ በአሁኑ ጊዜ ከሩሲያ ከበርቴዎችጋርች እና ከሌሎች ተቋማት 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር እንዳይንቀሳቀስ አድርገናል ያሉ ሲሆን ይህም በጣም ትልቅ ገንዘብ ነው ሲሉ ገልፀውታል፡፡
ከታገደው ገንዘብ መካከል ከ12 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚሆነው በአምስት አባል ሀገራት ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ የታገደ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በተያያዘም የአውሮፓ ኀብረት ለዩክሬን አንድ ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማፅደቁን አር ቲ ዘግቧል፡፡
በሌላ በኩል የኀብረቱ የገንዘብ ሚኒስትሮች በግንቦት ወር በአውሮፓ መሪዎች ስምምነት ለኪዬቭ ቃል ከተገባላት ዘጠኝ ቢሊየን ዶላር በጀት ውስጥ አንድ ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አፅድቋል።
ይህ ዩክሬን አስቸኳይ ፍላጎቶችን ለመሸፈን እና ወሳኝ የሆኑ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለማከናወን አስፈላጊውን እገዛ ያደርግላታል ሲሉ የአውሮፓ ህብረት ቀጣይ ፕሬዚዳንትነትን የሚይዙት የቼክ ሪፐብሊክ የገንዘብ ሚኒስትር ዚቢኔክ ስታንጁራ ተናግረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.