Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የዶራሌህ የእንስሳት ማቆያ ተርሚናልን ጥቅም ላይ ለማዋል ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የዶራሌህ የእንስሳት ማቆያ ተርሚናልን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ተርሚናሉ ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብት ቀዳሚ ሀገር እንደመሆኗ ሀብቷን በተገቢው መልኩ ወደ ውጭ እንድትልክ በማስቻል እና የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማስገኘት ከእንስሳት ሀብቷ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላታል ተብሏል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን እና የጂቡቲ አቻቸው ሙሀመድ አሕመድ መፈረማቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል ፡፡

አቶ ኡመር ሁሴን ጉዳዩን አስመልክቶ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ የዶራሌህ ሁለገብ ወደብ ወደ ስራ መግባቱ፥ ወደ ውጭ ለሚላኩ እንስሳት የማረፊያ ተርሚናል ሆኖ በማገልገል እና የቀጥታ ግብይትን በማበረታታት የኢኮኖሚ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.