Fana: At a Speed of Life!

ተጠብቀው የቆዩ ማኅበራዊ እሴቶች በትምህርት ሥርዓት ሊደገፉ እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ኢትዮጵያን ያሻገሩ እና በትውልዱ ተጠብቀው የቆዩ ማኅበራዊ እሴቶች በትምህርት ሥርዓት ሊደገፉ እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ፍልስፍና መምህሩ ዶክተር ተሾመ አበራ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የትናንት ትውልድ ዐሻራ የሆኑ የማኅበረሰቡ እውቀቶች ዛሬ በተለያየ ምክንያት በመሸራረፋቸው ባልተለመደ መንገድ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን የሚጋፉ ድርጊቶች እንዲታዩና እንዲሰሙ አድርጓል፡፡
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህርት ሊዲያ አዳነ በበኩላቸው÷ አሁን በሀገራችን እየተደረጉ ያሉ ለጆሮ የሚከብዱ ድርጊቶች ሊታረሙ የሚችሉት ትናንት አንድ ባደረጉን ጉዳዮቻችን ላይ ትኩረት በማድረግ እና የአሁኑን ትውልድ ማህበረሰባዊ እሴቱን ማውረስ ስንችል ነው ብለዋል።
ከገባንበት አዘቅት ለመውጣት ከሌሎች ሀገራት የተኮረጀው የትምህርት ሥርዓታችን በራሳችን አኩሪ እውቀቶች የታሸ መሆን ይገባዋል ሲሉ ምሁራኑ ይመክራሉ፡፡
መተኪያ የሌላት ሀገር በማህበረሰቡ ጤናማ እሳቤና አንድነት እንደምትገነባ ገልጸው÷ ማህበራዊ ሃብቶቻችን በክብር ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገሩ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.