Fana: At a Speed of Life!

በ2014 በጀት ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ወጪ ንግድ ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ወጪ ንግድ ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ከባለሀብቶችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት በበጀት አመቱ የተገኘው ገቢ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር የ100 ሚሊየን ዶላር ብልጫ አለው።
የኢንዱስትሪው ዘርፍ የተለያዩ ችግሮች ያሉበት ሲሆን በተለይም በግብአት አቅርቦት ፣ የውጭ ምንዛሬ፣ የአሰራር ችግር እና የክህሎት ማነስ እንደ ተግዳሮት የሚነሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ይህንን ለመፍታትም በጋራ መስራት ይገባል ነው ያሉት።
በሌላ መልኩ ዘርፉ በይበልጥ እንዳያድግ ማነቆ የሆነውን የፖሊሲ ችግር መፍታት መቻሉን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
በቅድስት ተስፋዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.