Fana: At a Speed of Life!

“ግሪን ትራንስፖርት” የተሰኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ስራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ግሪን ትራንስፖርት” የተሰኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ስራ ጀምረዋል።

ተሽከርካሪዎቹ “ግሪን ቴክ አፍሪካ” በተሰኘ ኩባንያ የተመረቱ ሲሆን÷ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተሽከርካሪዎቹን ስራ ዛሬ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ መርሐግብሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ የትራንስፓርት ዘርፉን ተደራሽና ፈጣን በማድረግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የትራንስፖርት ስርዓት ለመገንባት እየተሰራ ነው።

በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣውን የበካይ ጋዝ ለመቀነስ መንግስታት እየሰሩ እንደሚገኙና ኢትዮጵያም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስተዋወቅ ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሆነች ገልጸዋል።

ስራ የጀመሩት ተሽከርካሪዎች ለመዲናዋ ነዋሪዎች ለአንድ ወር ያህል ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተሽከርካሪዎቹ የተለያየ መጠን ያላቸውና የአየር ብክለትን በመቀነስ ለአካባቢ ጥበቃና ደህንነት ጉልህ ሚና አላቸው ነው የተባለው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.