Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያው “X5” ኩባንያ በኢትዮጵያ የሚመረቱ አበባዎችን መግዛት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግዙፉ የሩሲያ ምግብ አከፋፋይ ኩባንያ “X5” በኢትዮጵያ የሚመረቱ አበባዎችን መግዛት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

ኩባንያው ከኢትዮጵያ የሚገዛቸውን አበባዎች ወደ ሩሲያ በማስገባት የማከፋፈል ፍላጎት እንዳለውም ነው የተገለፀው።

ከኢትዮጵያ የሚገዙ አበባዎችም ፐይቴሮችካ እና ፐሬክረስቶክ በተባሉ የሞስኮ እና የቅዱስ ፒተርስበርግ አካባቢዎች ለሽያጭ የሚቀርቡ መሆኑም ታውቋል።

“X5” ኩባንያ በኢትዮጵያው አፍሪፍሎራ አክሲዮን ማህበር አማካኝነት የሚለሙ አበባዎችን እንደሚገዛም ነው ያስታወቀው።

በዚህም ኩባንያው አበባዎችን ቀጥታ ከአፍሪካ ወደ ሩሲያ በማስገባት ከሀገሪቱ ምግብ አከፋፋይ ኩባንያዎች ቀዳሚው አንደሚሆን ነው የተገለፀው።

ምንጭ፦ esmmagazine

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.