Fana: At a Speed of Life!

እስካሁን 50 ሺህ 337 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እስካሁን 50 ሺህ 337 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከመጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

ለሦስት ወራት ከ15 ቀናት በተደረገ ዜጎችን የመመለስ ስራም በ137 በረራዎች 50 ሺህ 337 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተመላክቷል፡፡

ከተመላሾች ውስጥ 37 ሺህ 485 ወንዶች፣ 9 ሺህ 225 ሴቶች እና 3 ሺህ 628 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እና ህፃናት መሆናቸው ነው የተገለጸው።

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀል ስራ ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ  ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.