Fana: At a Speed of Life!

ኦሮሚያ ባንክ “የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች” የ2022 አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ ባንክ “የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች” የ2022 አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆኗል።

ከተመሠረተ 14 አመት የሆነው የኦሮሚያ ባንክ በዓለም አቀፍ ንግድ እና ሁሉ አቀፍ የአገልግሎት ልሕቀት እንዲሁም እያከናወነ ያለውን የትራንስፎርሜሽን ተግባር ከግንዛቤ በማስገባት ነው ሽልማቱን ያገኘው፡፡

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ሽልማቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ÷ የአገልግሎት ጥራት ተሸላሚ መሆኑ ለኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ፋና ወጊና ተምሳሌት ከመሆኑም በላይ ለሀገር ኩራት መሆኑን ተናግረዋል።

በመላው ዓለም ከሚገኙ 35 ሀገራት የተውጣጡ 43 ድርጅቶች በሽልማቱ ላይ መሳተፋቸውን ጠቅሰው÷ በባንክ ደረጃ ከኢትዮጵያ ኦሮሚያ ባንክ የመጀመሪያው መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ካለችበት ዘርፈ ብዙ ተግዳሮት አንጻር በዚህ ወቅት ባንኩ ዓለም አቀፍ ሽልማት ማግኘቱ ለሀገርም ሆነ ለባንኩ መልካም ገፅታን የሚያላብስ ነው ብለዋል።

ሽልማቱ ለወደፊቱ በሀገሪቱ ፋይናንስ ዘርፍ ለሚጫወተው ሚናም በላቀ ትጋትና ጥራት ለመስራት መነቃቃትን ይፈጥራል ነው የተባለው።

የሽልማት አሰጣጣጥ ስነ-ስርዓቱ ሰኔ 26  እና 27 ቀን 2014 በስፔን ባርሴሎና የተካሄደ ሲሆን፥ ይህን ሽልማት ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሸለሙ ይታወሳል፡፡

በአለም ሰገድ አሳዬ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.