Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በ1 ጀምበር 250 ሚሊየን ችግኞች የሚተከሉበት መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ) በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር 250 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል አረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተካሄደ፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀንበር በስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት÷ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራው አንድ አካል የሆነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የውሀ ሀብትንም ለመጠበቅ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።

ህብረተሰቡ ጦርነቱ የፈጠረው የስነ ልቦና ጫና ሳይበግረው የተፈጥሮ ሀብት ስራ በስፋት ሲያከናውን መቆቱን ገልጸው÷ አሁን በፈተናዎች ውስጥ ሆነንም ቢሆን ይህን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሁን ላይ በአማራ ክልል እና ከክልሉ ውጭ እየተከሰቱ ባሉ የፀጥታ ችግሮች ወገኖች ሰለባ እየሆኑ ነው ያሉት ዶክተር ጌታቸው÷ ይህን ችግር ለመቀልበስ የውስጥ አንድነትን በማጠናከርና ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በቅንጅት በመስራት እነዚህን ጠላቶች መታገል ያስፈልጋል ብለዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው በበኩላቸው÷ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች 250 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል።

ችግኝ ተከላው ለኢኮኖሚው የሚኖረውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ከግምት በማስገባት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በትኩረት እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.