Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን የክልሉ የኢንቨስትመንት ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በክልሉ በተጠናቀቀው የ2014 በጀት ዓመት ለ81 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ89 ባለሃብቶች ባቀረቡት ፕሮጀክት አማካኝነት የኢንቨስትመንት ፍቃድ እንደተሰጣቸው የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ አስታውቀዋል፡፡

ከ1 ነጥብ4 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡት እነዚህ ባለሃብቶች፥ በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ ሆቴል፣ አገልግሎት፣ ሁለገብ የገበያ ማዕከላት፣ ግንባታ፣ እርሻ እና ግብርና ውጤቶች ማቀነባበር ስራዎች ለመሰማራት ባቀረቡት ፕሮጀክት የኢንቨስትመንት ፍቃዱ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በክልሉ በኢንቨስትመንት መስክ ለመሰማራት ፍቃድ የተሰጣቸው ባለሃብቶች ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በካፒታል መጠን በ300 ሚሊየን ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ግንባታ ጨርሰው ወደ ስራ ሲገቡም ከ3 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥሩም አቶ መሐመድ ገልጸዋል፡፡

ጽህፈት ቤቱ ለባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከመስጠቱም ባሻገር ለ129 ፕሮጀክቶች የክትትልና ድጋፍ መሰጠቱንና ከዚህ በፊት ፈቃድ ተሰጥቷቸውና መሬት ተረክበው ወደ ግንባታ ሳይገቡ ቆይተው የነበሩ 17 ፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉም ተገልጿል፡፡

ለረዥም ጊዜያት መሬት አጥረው ለተቀመጡ ለ18 ፕሮጀክቶች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ የቃልና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የገለጹት ሃላፊው ፥ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ወደ ስራ የማይገቡ ከሆነ የኢንቨስትመንት ፍቃዱን በመሰረዝ የተረከቡትን መሬት ወደ መሬት ባንክ የማስገባት እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.