Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩቶች ተሰራጩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ከዶሮ እርባታ ዘርፍ የሚገኘውን ሀብት ለማሳደግ ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩቶችን መሰራጨታቸው ተገለጸ፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያና መኖ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ እያሱ ተፈራ እንደገለጹት፥ የአርሶ አደሩን የዶሮ ልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤታማ ተግባራት ማከናወን ተችሏል።

ስርጭቱ ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በዶሮ እርባታ ዘርፍ የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ መሆኑን አንስተው ፥ የህብረተሰቡን ስርዓተ ምግብ ከማሻሻል ባለፈ በአሁኑ ሰዓት እየናረ ያለውን የዶሮ ምርት ገበያ ለማረጋጋት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ ባለፈው በጀት ዓመት በዶሮ እርባታ ዘርፍ ከ636 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውንም ኃላፊው አብራርተዋል።

ክላስተርን መሠረት ባደረገ የዶሮ እርባታ ከዘርፉ የሚገኘውን ምርት ከማሳደግ ባለፈ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያስችላል ሲሉ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.