Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር በትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የከተማዋ ትራንስፖር ቢሮ አስታወቀ፡፡
 
ቢሮው ከነገ ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ አድርጓል፡፡
 
በዚህ መሰረት፦
 
የሚኒባስ ታክሲ ዝቅተኛው በ2 በነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 3 ብር የነበረው ታሪፍ 3 ብር ከ50 ሳንቲም ሲሆን÷ ከፍተኛው ደግሞ ከ27 ነጥብ 6 እስከ 30 ኪሎ ሜትር 33 ብር 50 ሳንቲም የነበረው 39 ብር ከ50 ሳንቲም ተደርጓል፡፡
 
ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5 ኪሎ ሜትር 5 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው 6 ብር ከ50 ሳንቲም፣ ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 8 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው 10 ብር ሆኗል፡፡
 
ከ7 ነጥብ 6 እስከ 10 ኪሎ ሜትር 11 ብር የነበረው 13 ብር እንዲሁም ከ10 ነጥብ 1 እስከ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 14 ብር የነበረው 16 ብር መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል፡፡
 
በሚዲ ባስ ወይም የሃይገርና ቅጥቅጥ ላይ የተሻሻለው ታሪፍ እስከ 8 ኪሎ ሜትር 4 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው 5 ብር ሲሆን ÷ ከ24 እስከ 28 ኪሎ ሜትር 15 ብር የነበረው ደግሞ 17 ብር ተደርጓል፡፡
 
የሸገር እና አንበሳ ከተማ አውቶብስ የትራንስፖርት ታሪፍም በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የሚስተካከል መሆኑን ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.