Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለፌደራል ፖሊስ የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እንደሚያጠናክር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአቅም ግንባታ እና ለተልዕኮ ስኬት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ረገድ የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምርጫ የፍላጎት ገምጋሚ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ የ6ኛው ሀገራዊ የምርጫ ሂደት ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዕቅድ እየተመራ ከምርጫው በፊት፣ በምርጫ ወቅት እና ከምርጫ በኋላ ስላከናወናቸው ጉዳዮች ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
እንደ ሀገር እየተከናወኑ ባሉ የለውጥ ስራዎች ተቋሙ አቅሙን በማሳደግ ቀጣይ የምርጫ ሂደቶች የተሻሉና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆኑ እየሠራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም÷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የግብዓትና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
የቡድኑ መሪ ሰርጌ ጋከዋንዲ ከብዊማና በበኩላቸው÷ በየደረጃው በሚደረጉ ምርጫዎች የፖሊስ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ፖሊስ ለምርጫው መሳካት ላበረከተው አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይም በየደረጃው ለሚደረጉ ምርጫዎች ዲሞክራሲያዊነት መስራት ይገባል ማለታቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተጨባጭ እያከናወነ ለሚገኛው ለውጥ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው÷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአቅም ግንባታና ለተልዕኮ ስኬት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጎን መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.