Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነገ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜና 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል፡፡

የምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ እንደገለጹት÷ ምክር ቤቱ በስብሰባው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

በተለይም የድጎማና በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴን፣ የማንነት አስተዳዳር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴን፣ የሕገ መንግስት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻጸም ክትትልና የመንግሥታት ግንኙነትና ዴሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ መንግስትን አስተምህሮ የ2014 በጀት ዓመት የአፈጻጻም ሪፖርት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ውስን ዓላማ ያላቸውን የድጎማ በጀትንና የፌዴራል መሰረተ ልማት ስርጭትን ፍትሐዊነት ለማስፈጸም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ በስፋት እንደሚወያይም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በተባሉ የውሳኔ ሀሳቦችና ለምክር ቤቱ በይግባኝ በቀረቡ አቤቱታዎችና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍም ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.