Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊታችን ሀገር ጠባቂ ብቻ ሳይሆን የልማት ኃይል መሆኑን በተግባር እያሳየ ነው- ሌ/ል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠራዊታችን ሀገር ጠባቂ ብቻ ሳይሆን የልማት ኃይል መሆኑን በተግባር እያሳየ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል አራተኛ ዙር ተቋማዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን “ማጽዳት፣ማስዋብ አና ማልማት” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።

በዛሬው እለት የተቋሙን ቅጥር ግቢ የማጽዳትና የማስዋብ ስራ የተካሄደ ሲሆን÷ በዋናነት ደግሞ በግብርና ሥራ የስንዴ ዘር የመዝራት ስራ ተከናውኗል።

የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ÷ በተቋሙ የሚገኘውን ሰፊና ለም መሬት ለማልማት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው÷ በዚህም የሠራዊቱን ኑሮ ለመደጎም መታቀዱን ጠቅሰዋል።

ከሠራን፣ ከለፋን ሀገራችንን መቀየር እንችላላን ያሉት ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ÷ እንደ ሠራዊት የተሰጠን ተልዕኮ ሀገርን የመጠበቅና መከላከል ቢሆንም የተሰጠንን ጊዜ ተጠቅመን ማልማት ይገባናል ብለዋል።

ሠራዊቱ የሀገርን ዳር ድንበር አስከባሪ ብቻ ሳይሆን የልማት ኃይል መሆኑንም አውስተዋል፡፡

የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከል የሆኑት ብርጋዴር ጀኔራል ኃይሉ መኮንን በበኩላቸው÷ከአሁን ቀደም ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ረገድ ተቋሙ ውጤታማ ስራ እንዳከናወነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.