Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት” በሚል መሪ ሀሳብ የአስተዳደሩ  የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ በሃይማኖት አባቶችና አባገዳ ምርቃት ተጀምሯል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፣ የደሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከደር ጁሀር፣ አምባሳደር መሀሙድ ድሪር፣ ዶክተር አሊ ቢራ፣ አባገዳዎችና ኡጋዞች እዲሁም ባለሀብቶች ተገኝተዋል።

በአጠቃላይ በመርሐ ግብሩ ላይ ከ300 በላይ እንግዶች መታደማቸውን ከድሬዳዋ ከተማ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.