Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ በግፍ ለተጨፈጨፉ ንጹሀን ዜጎች የህሊና ጸሎት በማድረግ ጉባኤውን የጀመረ ሲሆን÷ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ውይይቱን ቀጥሏል።
በቀጣይም የአራቱን ቋሚ ኮሚቴዎች እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤን የ2014 ዓ.ም የአፈጻጸም ሪፖርቶች፣ ከሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በተባሉ የውሳኔ ሐሳቦች፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በሚል ውሳኔ በተሰጣቸው እና ለምክር ቤቱ በይግባኝ በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1261/ 2013 ለማስፈጸም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ፣ ውስን ዓላማ ያላቸው የድጎማ በጀትና የፌዴራል መሠረተ ልማት ስርጭት ፍትሐዊነት የክትትል ሥርዓትን ለማስፈጸም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተለያየዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅም ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.