Fana: At a Speed of Life!

እህል ከዩክሬን ለዓለም ገበያ በሚቀርብበት አግባብ ላይ ሥምምነት ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ፣ ዩክሬን፣ ቱርክ እና የተመድ ባለሥልጣናት የምግብ እህል ከዩክሬን በጥቁር ባሕር በኩል ለዓለም ገበያ በሚቀርብበት አግባብ ላይ ተሥማምተዋል፡፡

የቱርክ መከላከያ ሚኒስትር ሁሉሲ አካር ረቡዕ ዕለት እንዳስታወቁት ÷ ሀገራቱ እና የተመድ ባለሥልጣናት የወጪንግድ ማስተባበሪያ ማዕከል ለማቋቋም እና ተቋርጦ የቆየው የዩክሬን እህል ወጪ ንግድ በድጋሚ በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ተደርሷል።

ሁሉሲ አካር በመግለጫቸው ቱርክ በማስተባበሩ በኩል የሚጠበቅባትን ሁሉ እንደምትወጣና በሚቀጥለው ሣምንትም ሁሉም ወገኖች በድጋሚ ተገናኝተው የሥምምነት ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ አስታውቀዋል፡፡

በሚቋቋመው የወጪ ንግድ ማስተባበሪያ ማዕከል በኩልም ተዋዋይ ወገኖች በጥቁር ባሕር ወደቦች ያለውን እህል የመቆጣጠር እና የመፈተሸ ሥራ በጋራ እንደሚያካሂዱ መሥማማታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው ÷ ሥምምነቱ በወጪ ንግድ ከዩክሬን ሲቀርብ የነበረውን እህል በድጋሚ ለማስጀመር “ወሳኝ እርምጃ” ሲሆን “የዛሬው መልካም ሂደት እንዳይጨናገፍ አሁንም ተጨማሪ ሥራዎች መሥራት ያስፈልጋል” ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.