Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ወደ ትግበራ ለማስገባት የተሠራው ሥራ ውጤታማ መሆኑን ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ ለማስገባት በተሠሩ ሥራዎች ውጤታማ ለውጥ መታየቱን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡

በክልሉ ትምህርት ቢሮ የአዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ተግባራትን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በውይይ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በሀገራችን እንዲሁም በክልላችን በሙከራ ደረጃ የተጀመረውን አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ወደ ትግበራ ለማስገባት በተሠሩ ሥራዎች አመርቂ ውጤቶች ታይተዋል፡፡

በቀጣይ በሚሠሩ ሥራዎችም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ስምዖን እንደገለጹት÷ በሙከራ ወቅት አስቸጋሪ ሁኔታዎችንና ጊዜን በማሳለፍ በተሠሩ ሥራዎች ሁሉም የሚጠበቅበትን ተወጥቷል፡፡

በኢብራሂም ባዲ እና መለሠ ታደለ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.