Fana: At a Speed of Life!

በታንዛኒያ ምንነቱ ባልታወቀ ህመም ሶስት ሰዎች ለኅልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህመሙ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ድካም እና ነስር እንደሚስከትል የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

እስካሁን በህመሙ ሳቢያ በደቡብ ምስራቅ ታንዛኒያ ሶስት ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 10 ሰዎች መታመማቸውም ነው የተገለጸው።

ምልክቶቹ እንደ ኢቦላ እና ማርበርግ ቫይረስ አይነት ከባድ ትኩሳት ቢኖራቸውም ታማሚዎቹ ላይ በተደረገ ምርመራ ግን ሁሉም ኮቪድ19ኝን ጨምሮ ከሁሉም ቫይረሶች ነጻ መሆናቸውም ተገልጿል።

በመንግስት የሚደገፍ የባለሙያዎች ቡድን በጉዳዩ ላይ እየሰራ እንደሚገኝም ታውቋል።

በደቡብ ምስራቅ ሊንዲ ክልል ውስጥ በተከሰተው ምነነቱ ያልታወቀ ህመም ከተያዙት 13 ሰዎች መካከል እስካሁን አንድ ሰው ብቻ ማገገሙን የአካባቢውን ባለስልጣናት ዋቢ ያደረገው የ ቲ አር ቲ ዘገባ ያመላክታል።

ባለፈው ሳምንት በጋና የማርበርግ ቫይረስ ሳይገኖርባቸው አይቀርም የተባሉ ሁለት ሰዎች ተገኝተዋል።

በንክኪና በሰውነት ፈሳሽ የሚተላለፈው የማርበርግ ቫይረስ ከፍተኛ ትኩሳት የሚያስከትልና በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 88 በመቶዎችን ለህልፈት የሚዳርግ ገዳይ ቫይረስ መሆኑ ይነገራል።

ቫይረሱ በምዕራብ አፍሪካ ሃገራት እምብዛም ያልተለመደ ሲሆን ጋና እና ታንዛኒያ ካላቸው ርቀት አንጻርም ሶስት ሰዎችን ለህልፈት ከዳረገው ህመምጋር ግንኙነት ላይኖረው ይችላል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.