Fana: At a Speed of Life!

ተወዳዳሪ የዲጂታል ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር እየተሠራ ነው – የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲጂታሉ ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ የሚሆን የዲጂታል ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ከተባበሩት መንግስታት የካፒታል ልማት ፈንድ ጋር በመተባበር በዲጂታል ክህሎት ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር መክሯል፡፡
መድረኩ ስለዲጂታል ክህሎት ዜጎችና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ በዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ የሚሆን የዲጂታል ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር እየተሠራ ነው፡፡
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ውስጥ የሰው ኃይል አቅምን የዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረት አድርጎ አስቀምጧል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ የዲጂታል ክህሎት ስትራቴጂ በመቅረፅ፣ የተለያዩ የዲጂታል ትምህርት እና ስልጠና አማራጮችን ለዜጎች በማቅረብ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፉ የቢዝነስ ማሽን ኮርፖሬሽን “በዲጂታል አፍሪካ ማህበረሰብ” ፕሮግራሙ ስር በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ለወጣቶች እና ለሴቶች እየሰጠው ባለው ስልጠና ከ1ሺህ 200 በላይ ሰልጣኞች ተሳትፈዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.