Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገነቡ ሕንፃዎችን ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የተገነባውን “80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት” ለአካባቢው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች በዕጣ አስተላልፈዋል፡፡

ሕንፃዎቹ ለነዋሪዎቹ የተላለፉት ነዋሪዎቹ ቀደም ሲል እንደ ነበራቸው የመኖሪያ ቤት ሥፋትና መጠን መሠረት ነውም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ከንቲባዋ በልቤ ፋና ትምህርት ቤት በመገኘት ያስገነቧቸውን ሁለት ተጨማሪ ሕንጻዎች ማስረከባቸውን ከከንቲባ ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.