Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከዓለም አቀፉ የማላመድ ማዕከል ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከዓአለም አቀፉ የማላመድ ማዕከል (ጂሲኤ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር ፓተሪክ ቨርኩጅን ጋር በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ኢትዮጵያ ብሄራዊ የማላመድ እቅድ አዘጋጅታ እየተገበረች መሆኗን አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ እንደ አገር እና አፍሪካ እንደ አህጉር ለአየር ንብረት ለውጥ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ቢሆንም በአየር ንብረት ለውጥ የሚደርስባቸው ተፅዕኖ ግን ከፍተኛ መሆኑን ፕሬዚዳንቷ አብራርተዋል፡፡
ዓለም አቀፉ የማላመድ ማዕከልእና የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ መላመድ የማፋጠን ፕሮግራም ለመደገፍ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማሰባሰብ እየሰሩ እንደሆነ መገለጹንም ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.