Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የሰሜን ኮሪያ ኤምባሲ  ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልግ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  በኢትዮጵያ የሰሜን ኮሪያ ኤምባሲ  ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልግ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የሰሜን ኮሪያ አምባሳደር ቶንጉ ሲም  ዛሬ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ጎበኝተዋል።

አምባሳደር ቶንጉ ሲም  በጉብኝታቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በይዘት እና በቴክኖሎጂ የገነባውን አቅም  ተመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ለሁለት አመት ተኩል የቆዩት አምባሳደሩ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባሉት የስርጭት ዓይነቶች በሀገሪቱ ቀዳሚ  ሚዲያ መሆኑን መታዘባቸውን ገልጸዋል ።

በሀገራት መካከል ያለን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ሚዲያ ትልቅ ሚና አለው ያሉት አምባሳደሩ፥ ለዚህ ኤምባሲያቸው ከፋና ጋር በትብብር ለመስራት መምረጡን አስታውቀዋል ።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በበኩላቸው ፋና እንደ ተቋም ከሰሜን ኮሪያ ኤምባሲ ጋር  በትብብር መስራት በሚቻልባቸው መስኮች ሁሉ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

በተለይ የቴክኖሎጂ ልውውጥ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክር ስራ የትብብሩ ትኩረት እንደሚሆን ነው ያስታወቁት።

 

በአልአዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.