Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጉባኤ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል፡፡
 
ምክር ቤቱ በጉባኤው የከተማ አስተዳደሩን የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትእና በከተማ አስተዳደሩ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት ዘገባ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ በ2015 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የበጀት እና ሌሎች ልዩ ልዩ አዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ከአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.