Fana: At a Speed of Life!

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ዮናስ ገዳ የ2022 የአልዛይመር አዋርድን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኒውሮ ሳይካትሪስት ፕሮፌሰር ዮናስ ገዳ የ2022 የአልዛይመር አዋርድን አሸንፈዋል፡፡

በጆርናል ኦፍ አልዛይመር ዲዚዝ በተሰኘው ዓለም አቀፍ ጆርናል በሚዘጋጀው ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ስራ በአልዛይመር ወይም የመርሳት ችግር ላይ ከተሰሩ ጥናቶች የፕሮፌሰሩ የላቀ ሆኖ በመገኘቱ ነው የዘንድሮ ተሸላሚ የሆኑት፡፡

ፕሮፌሰር ዮናስ ገዳ በዶክተር ኦፍ ሜዲስን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን÷ ለ25 ዓመታት አሜሪካ  በሚገኘው ማዮ ክሊኒክ ውስጥ ሲያገለግሉ ቆይተው በአሪዞና ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን አግኝተዋል፡፡

የተመረጠው ጥናት ባለቤት የሆኑት ፕሮፌሰሩ 7 ሺህ ዶላርና የብር ሜዳሊያ ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን÷  የሽልማት ስነ-ስርዓቱም በቀጣዩ ነሐሴ ወር እንደሚካሄድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.