Fana: At a Speed of Life!

የሎተሪ ትኬትን በዲጂታል አማራጭ ማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የሎተሪ ትኬት በዲጂታል አማራጭ ማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ ፡፡
የብሔራዊ ሎተሪ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገረመው ጋርጄ ስምምነቱ በተደረገበት ጊዜ እንዳሉት ፥ አስተዳደሩ ባለፋት 60 ዓመታት ሎተሪን ለደንበኞች ለማድረስ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው፥ በአሁኑ ወቅት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች የሎተሪ ቲኬት በቀላሉ መቁረጥ የሚያስችላቸውን የዲጂታል ሎተሪ ማቅረብ ችለናል ብለዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው ፥ የዲጂታል ሎተሪ አማራጭ በርካታ ደንበኞች እንዲጠቀሙ አገልግሎቱን በቅርብና በፍጥነት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።
አድማስ ሎተሪ የተሰኘው የዲጂታል ሎተሪ በቴሌብር አልያም በ605 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መግዛት እንደሚቻል ፤ ክፍያው ከተፈጸመ በኋላም የክፍያ ደረሰኝ እንደሚልክ እና ከአንድ በላይ ትኬት ለመግዛት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው።
በቅድስት አባተ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.