Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማቱ አመራሮችና ሠራተኞች በኦሮሚያ ክልል ችግኝ ተከከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች በኦሮሚያ ክልል አቃቂ ወረዳ ቢልቢሎ ተራራ ችግኝ ተክለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የቢልቢሎ ተፋሰስን ለማልማት በወሰደው ኃላፊነት÷ ላለፉት ዓመታት ችግኝ የመትከልና አካባቢውን የማልማት ሥራ ሲሠራ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

በዛሬው ዕለት “አረንጓዴ ዐሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ሀሳብ የተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም የእዚሁ አካል ነው ተብሏል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት÷ ለአካባቢው ስነ ምህዳርና የአየር ጸባይ ተስማሚ የሆኑ እንዲሁም የአፈር መሸርሸርን መቋቋም የሚችሉ ችግኞች ተተክለዋል፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሩ የአየርንብረትን በማስተካከልና የተፈጥሮ ሃብቱን በመጠበቅ ለግብርና ሥራው የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመው÷ ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ አፈወርቅ በበኩላቸው÷ በክልሉ ባለፉት ዓመታት 9 ቢሊየን ችግኝ መተከሉን ገልጸው ዘንድሮም 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ችግኖችን ለመትከል ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ነሐሴ 11 ቀን 2014 ደግሞ በክልሉ በአንድ ቀን 400 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል መታሰቡን አመላክተዋል፡፡

በሃይማኖት ኢያሱ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.