Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ያደረገችው ጥረት በአርዓያነት ሊወሰድ የሚችል መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትሯር ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ያደረገችው ጥረት በመልካም ተሞክሮ ሊወሰድ የሚችል ነው ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትሯር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ገለጹ፡፡

በኒዉዮርክ የተካሄደው የአገራት በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የዘላቂ የልማት ግቦች ዳሰሳ ላይ ኢትዮጵያ የስድስት ዓመታት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር አፈጻጸሟን አቅርባለች፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ÷ ኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮችና ፈተናዎች ውስጥ ብትሆንም የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በከፍተኛ ኃላፊነት እየሰራች ትገኛለች ብለዋል፡፡

17ቱን የዘላቂ ልማት ግቦች ለማሳካት ያደረገችው ጥረት በመልካም ተሞክሮነት ሊወሰድ የሚገባው መሆኑን ነው ሚኒስትሯ ለመድረኩ ያስረዱት፡፡

ድህነትን መዋጋት ፣ የኢኮኖሚ እድገትን በማፋጠንና የነፍስ ወከፍ ገቢን በማሳደግ፣ የዜጎችን የገቢ ልዩነት በማጥበብና በሌሎች የኢኮኖሚያና ማህበራዊ መስኮች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑንም ሚኒስትሯ አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያን ያጋጠማት ጦርነት ፣ የአየር ንብረት ለውጥ የፈጠረው ተጽዕኖ እና ያስከተለው ድርቅ፣ ጎርፍና የበረሃ አንበጣ እንዲሀም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ለግቦቹ ስኬታማነት ተግዳሮት እንደነበሩም ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአገራት የዘላቂ ልማት ግቦች የዳሰሳ ሪፖርት በአውሮፓውያኑ 2017 አቅርባ እንደነበርም ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.