Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግስት ትርጉምን አስመልክቶ የቀረቡ የውሳኔ ሀሳቦችን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄን አስመልክቶ በቀረቡ የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ አፀደቀ፡፡
ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥት ጉዳዩች አጣሪ ጉባዔ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል በቋሚ ኮሚቴው ተጠንተው ከቀረቡ ሰባት የውሳኔ ሀሳቦች መካከል÷ ስድስቱን “የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም” በሚል እና አንዱን የውሳኔ ሀሳብ “የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል” በሚል በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
በተጨማሪም÷ቋሚ ኮሚቴው አጣሪ ጉባዔ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በሚል ውሳኔ በተሰጣቸውና ለምክር ቤቱ በይግባኝ በቀረቡ 80 አቤቱተታዎች ላይ ተወያይቶ “የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም” በሚል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በአንድ ድምፅ ተዕቅቦ በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁን ከፌዴሬሽን ምክርቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.