Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ተጠባባቂ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሁለትዮሽ እና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮችን በሚመለከት ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ተጠባባቂ ሚኒስትር ባላል ሞሀመድ ኦስማን ጋር ተወያዩ ፡፡

በውይይታቸውም÷ የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት በትብብር የሚሰሩባቸው በርካታ መስኮች መኖራቸውን አስታውሰው ፤ በተለይ ፀረ ሽብር ዘመቻ ላይ ያላቸውን እንቅስቃሴ ማጠናከር እንደሚገባ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ሶማሊያ የተሳካ ምርጫ እና የመንግሥት ምሥረታ በማካሄዷየተሰማቸውን ደስታ ለተጠባባቂ ሚኒስትሩ ገልፀውላቸዋል።

ተጠባባቂ ሚኒስትሩ ሞሀመድ ኦስማን በበኩላቸው ፥ አዲሱ የሶማሊያ መንግስት በሀገሪቱ ሰላምን ለማስፈን ልዩ ትኩረት እንደሰጠና በዚህም ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

አልሸባብ የሽብር ቡድንን ለማጥፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሁለቱ ሀገራት ህብረት መጠናከር እንዳለበትም አመልክተዋል።

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የሁለትዮሽ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በቅርቡ ለማካሄድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.