Fana: At a Speed of Life!

ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል ተወሰነ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል ወስነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ እስካሁን የተቋረጡ ትምህርቶችን በማካካስ የሕክምና ትምህርቱን ካቆመበት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

የተማሪ ቢንያም ኢሳያስን ትምህርት በተመለከተ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የሕክምና ትምህርት ቤት ለተማሪው የትምህርት ሂደት ይረዳሉ ያሏቸውን አማራጮችን ቢያቀርቡም ÷ ተማሪ ቢንያም ብቸኛ ፍላጎቱ የሕክምና ትምህርትን መማር እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁም መሠረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል ተወስኗል።

እስካሁን የተቋረጡ ትምህርቶችንም በማካካስ ትምህርቱን ካቆመበት እንዲቀጥል ይደረጋል መባሉን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንም እንኳን የትምህርት ሂደቱ ከባድ እና ውስብስብ ቢሆንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የሕክምና ትምህርት ቤቱ የተማሪ ቢንያምን ትምህርት የተሳካ እንዲሆን የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.