Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ናሚቢያ  የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ምክክር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ናሚቢያ እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ ህብረት አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ምክክር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የናሚቢያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዓለምአቀፍ ግንኙነት  ሚኒስትር  ኔቱምቦ ናንዲ  ናቸው የፈረሙት፡፡

ከፊርማ ስነ ስርአቱ በፊት በነበረው ውይይት  አቶ ደመቀ መኮንን ባደረጉት ንግግር÷  ኢትዮጵያ በናሚቢያ ይካሄድ የነበረውን የፀረ አፓርታይድ ትግል ትደግፍ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ናምቢ ከአፓርታይድ ስርዓት ነፃ ከወጣች በኋላም÷ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸው እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የዛሬው ስምምነትም÷ ሀገራቱ ታሪካዊውን ግንኙነታቸውን በተለያዩ መስኮች እንዲያሰፉ እና  አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያስችል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ ወቅታዊ  ሁኔታ ላይ  ባደረጉት ገለጻ÷ መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ አፍሪካውያን ወዳጅ ሀገራት ላሳዩት ተነሳሽነት አመስግነዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላት ገልጸው÷ ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ጉዳይም በሰላም ለመፍታት መንግስት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

ኔቱምቦ ናንዲ በበኩለቸው÷ ኢትዮጵያ በናሚቢያውያን ላይ የነበረውን የአፓርታይድ ጭቆና በመታገል ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረጓን አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ÷የናቢያን ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  እንዲቀርብ ማድረጓ የናሚቢያውያን ሕዝብ ትግል ይበልጥ እንዲጠናከር የላቀ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.