Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ ስራ ለማስገባት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወደ ልዩ ነፃ የንግድ ቀጠና ለማሻገር የሚያስችሉ የአገልግሎትና የመሰረተ ልማት ማሻሻያዎችን በፍጥነት የማሟላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገልጿል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ÷ በድሬ ዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ነጻ የንግድ ቀጠናን ለማስጀመር እየተከናወኑ የሚገኙ የአገልግሎትና የመሰረተ ልማት ስራዎችን ተመልክተዋል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ነጻ የንግድ ቀጠናውን ለማስጀመር የሚያስችሉ የመሰረተ ልማት፣ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ያሉበትን ደረጃ ከተመለከቱ በኋላ በቀጣይ መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ነጻ ንግድ ቀጠናው ለፓርኩ ተጨማሪ አቅምን የሚፈጥርና በፓርኩ ውስጥ የሚገቡ ባለሃብቶችን ፍሰት የሚጨምር በመሆኑ ስራዎች በፍጥነት እየተከነወኑ ቢሆንም÷ ቀሪ ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ ስራ ለማስገባት ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

ለተግባራዊነቱም ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.