Fana: At a Speed of Life!

በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ የገባ ከ9 ሺህ በላይ የሽጉጥ ጥይቶች ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የገባ ከ9 ሺህ በላይ የሽጉጥ ጥይቶች ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተያዙ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ መነሻውን ባህርዳር ከተማ ያደረገ ኤፍኤስአር ተሽከርካሪ ከጫት ጋር በማዳበሪያ ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ የገባ 9 ሺህ 950 የሽጉጥ ጥይት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አጂፕ ቶታል አካባቢ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ከእነ ተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍንጅ መያዛቸን አስታውቋል፡፡

ጥይቱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣሪዎች እና ለሕገ ወጥ ተግባር የተገለገሉበት አንድ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው መቀጠሉንም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ህገ-ወጥ ተግባር በማጋለጥ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካለት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.