Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ አስተዳደር ለ24 ዘመናዊ ሆስፒታሎች ግንባታ የሚውል መሬት መስጠቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ተደራሽ ለማድረግ ለ24 ዘመናዊ ሆስፒታሎች ግንባታ የሚውል መሬት መስጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጤና ዘርፍ የተሠሩትን ሥራዎች ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርታቸውም÷ የእናቶች እና የሕጻናት ሞትን ለመቀነስ በወሊድ ጊዜ በባለሙያ የታገዘ የወሊድ አገልግሎት ለ152 ሺህ 990 እናቶች በባለሙያ የታገዘ የወሊድ አገልግሎት መሰጡትን ጠቅሰው÷ የድህረ ወሊድ ክትትል ለማድረግ ለ156 ሺህ 94 የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በማድረግ የእናቶችን ሞት መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ሽፋንም 81 ነጥብ 3 በመቶ ማሳካት መቻሉን ከንቲባዋ አብራርተዋል።

ከፍለው መታከም ለማይችሉ ወገኖች 83 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ 28 ሺህ 882 የቤተሰብ አባላት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉንም አንስተዋል፡፡

የመድሀኒትና የህክምና መሳሪያዎች መናር ጋር በተያያዘ ከከተማ አስተዳደሩ በጀት 181 ነጥብ6 ሚሊየን ብር ድጎማ መደረጉንም ነው ገለጹት፡፡

የኩላሊት ህክምና የተደራሽነትና የአቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ÷ ከአጋር ድርጅት ጋር በመሆን 30 አዳዲስ የኩላሊት እጥበት ማሽኖችን በማስገባት በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ሥራ መጀመሩን ጠቁመው÷ ይህም የከተማውን የኩላሊት እጥበት አቅም በአምስት እጥፍ ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ከተማ አስተዳደሩ አቅም ለሌላቸው የኩላሊት እጥበት ለሚያስፈልጋቸው ህሙማንን ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመሸፈን ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡

የጤና ቱሪዝምን ለማሳደግና አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ተደራሽ ለማድረግ ለ24 ዘመናዊ ሆስፒታሎች ግንባታ የሚውል መሬት አዘጋጅተን በመስጠት ድጋፍ የማድረግ ሥራ ሰርተናል ብለዋል ከንቲባ አዳነች፡፡

ይህም ከውጭ ኢንቨስትመንት በተጨማሪ የሀገር ውስጥ አልሚዎችና ጤና ባለሙያዎች ለማበረታታት የከተማ አስተዳደሩ ባለው ቁርጠኝነት መሰረት የጤና መሰረተ ልማት ጥያቄን መሰረት በማድረግ÷ ለአዲስ ጤና ተቋማት 13 ለነባር ማስፋፊያ 11 በአጠቃላይ 24 ቦታዎች በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ማለታቸውንየከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.