Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ሰላምና እርቅ እንዲስፋፋ በማድረግ ረገድ  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ትልቅ ሚና አላቸው-ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ሰላምና እርቅ እንዲስፋፋ በማድረግ ረገድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ትልቅ  ሚና እንዳላቸው የፍትሕ ሚኒስተር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ ፡፡

አምስተኛው የኢፌዴሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጉባዔ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንደገለፁት÷ ከሦስት ዓመታት በፊት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን የሚያስተዳድር የሕግ ማዕቀፍ ለማሻሻል ጥረት ተድርጓል፡፡

አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የሚመለከት አዋጅ የፀደቀ ቢሆንም ብቻውን ስኬታማ መሆን ስለማይችል ከክልሎች ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የፌደራል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ  በበኩላቸው÷ባለስልጣኑ  ከፍትሕ ሚኒስቴር የተሰጠውን አዋጅ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተለያዩ መመሪያዎችን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

አዋጁን ለመተግበር ባለስልጣኑ በርካታ መመሪያዎችን ያዘጋጀ ሲሆን÷ ባለፋት ጊዜያቶችም  ዘጠኝ መመሪያዎችን በቦርድ ማፀደቅ መቻሉንና ተጨማሪ  ስምንት መመሪያዎች ደግሞ በሒደት ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

በፌዴራል ደረጃ የወጡ ህጎች ወደ ክልል የሚወርዱባቸውን ሁኔታ ላይ ፍትሕ ሚኒስቴር የድጋፍ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.