Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ከተመድ ሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋም ጋር ስምምነት ተፈራርመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በተመድ ሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋም ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት በስራ ላይ የሚውልና የስራ ግንኙነታቸውን የሚያጠናክር የመግባቢያ ሰነድና የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራርሙ፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬና በተመድ የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋም ምክትል ተወካይና ጊዜያዊ ዋና ተጠሪ ሻድራክ ዱሳቤ መካከል ነው፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ የተመድ የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋም ከሚኒስቴሩ ጋር የረዥም ጊዜ የስራ ግንኙነት ያለውና ስትራቴጂክ አጋር መሆኑን ጠቁመው፥ በሴቶች ጉዳይ ላይ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን በጋራ መስራታቸውን ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም የመግባቢያ ሰነዱና ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን የ10 ዓመት መሪ እቅድ እንዲሁም የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሚኒስትሯ፥ የመግባቢያ ሰነዱ በሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ማስወገድና ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ የማስቻልና የሴቶችን አመራርና ውሳኔ ሰጪነት ሚና በሁሉም ዘርፍ ማጎልበት እንደሚያስችል አስረድተዋል።

ሴቶችና አደረጃጀቶቻቸው በሰላም ግንባታና ሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥ ላይ በውሳኔ ሰጪነት እንዲሳተፉ የማስቻልና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ስራዎችን የማጠናከር እና አቅም የመገንባት አቀጣጫዎች እንዳሉትም ገልጸዋል።

ከተቋሙ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ቢሮ ዳይሬክተር ዶ/ር ማክሲም ሀዊናቶ በበኩላቸዉ ፥ ሴቶችን በተለይ በኢኮኖሚና በውሳኔ ሰጪነት ለማብቃት እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በከፍተኛ ቁጥር እንዲሰማሩ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው ያረጋገጡት፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.